Ethiop. J. Agric. Sci. 30(1) 87-97 (2020) Virulence Spectrum of Puccinia graminis f. sp. tritici in Northwest Ethiopia Yehizbalem Azmeraw1*, Belayneh Admassu2, Bekele Abeyo3, and Netsanet Bacha4 1 School of plant sciences, Haramaya University, P.O. Box 138, Dire Dawa, Ethiopia 2University of Idaho, Dept. of Entomology, Plant Pathology and Nematology, Aberdeen Research and Extension Center, 1693 S 2700 W, Aberdeen ID 83210, USA 3International Maize and Wheat Improvement Center, P.O. Box 5689, Addis Ababa, Ethiopia 4Ambo Agricultural Research Center, P.O. Box 37, Ambo, Ethiopia *Corresponding Author email:
[email protected] አህፅሮት ኢትዮጵያ ውስጥ ስንዴን ከሚያጠቁ በሽታዎች መካከል የግንድ ዋግ አንዱ እና ዋነኛው ነው፡፡ ይህንን በሽታ የሚያመጣው ተዋስያን አካል የአየሩን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም እራሱን እየቀያየረ በሽታ የሚቋቋሙ የስንዴ ዝርያዎችን በማጥቃት ከፍተኛ የሆነ የምርት ቅነሳ ያደርጋል፡፡ የዚህ ጥናት ዓላማ የነበረው በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የስንዴ የግንድ ዋግ ዝርያ መለየት ነው፡፡ ሰማንያ ስድስት ናሙናዎች በ2010 እና በ2011 የምርት ዘመን ተሰብስበው 20 ድፍሬንሻሎችን በመጠቀም አራት (TTTTF, TKTTF, TKPTF, and TTRTF) የስንዴ ግንድ ዋግ ዝርያዎችን ለመለየት ተችሏል፡፡ ከእነዚህ አራት ዝርያዎች ውስጥ በ2010ና በ2011 በተከታታይ በአማካይ በመቶኛ TTTTF 60.4 እና 60 የሚሆነውን የሚሸፍን ሲሆን በሁለተኛነት ደረጃ TKTTF 38.7 እና 37.3 ሸፍኖ ታይቷል፡፡ ሌሎች የግንድ ዋግ ዝርያዎች በሁለቱም የምርት ዘመን በአማካይ በመቶኛ 1 የሚሆነውን የሸፈኑ ሲሆን እነዚህ ሁለት ዝርያዎች የተገኙትም፤ TKPTF በ2010 ከደቡብ ጎንደር ፋርጣ ሲሆን TTRTF በ2011 ከሰሜን ጎንደር አምባ ጊዎርጊስ ላይ ብቻ ነው፡፡ የግንድ ዋግ የሚቋቋሙ ዘረመልን የያዙ ድፍሬንሻሎች እንደ Sr5, Sr21, Sr9e, Sr7b, Sr6, Sr8a, Sr9g, Sr36, Sr17, Sr9a, Sr9d, Sr10, SrTmp, Sr38 እና SrMcN ሁሉም በተለዩ የዋግ ዝርያዎች የተጠቁ ሲሆን Sr24 እና Sr31 ዋግ የሚቋቋሙ ዘረመልን የያዙ ድፍሬንሻሎች ግን ሙሉ በሙሉ የተለዩትን የዋግ ዝርያዎችን መቋቋም ችለዋል፡፡ በአሁኑ ጥናት Sr31 እና በአሁኑና ከዚህ በፊት ኢትዮጵያ ውስጥ በተደረጉ ጥናቶች Sr24 ዘረመልን የሚያጠቃ የግንድ ዋግ ዝርያ ያለመኖሩ ስለተረጋገጠ እነዚህን ዘረመሎች ከሌሎች የግንድ ዋግ መቆጣጠሪያ መንገዶች ጋር በመጠቀም አሁን ያለውን የግንድ ዋግ ዝርያ መቋቋም የሚችል የስንዴ ዝርያ ማዳቀል ይቻላል፡፡ Abstract Stem rust caused by Puccinia graminis f.